የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

By amele Demisew

August 24, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የከተማው ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡፡ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ50 ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ6ቱ ህይወት አልፏል፡፡ ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡