የሀገር ውስጥ ዜና

የመውሊድ በዓል በጅማ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

By Hailemaryam Tegegn

August 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 1ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል (መውሊድ) በጅማ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡

በዓሉ በጅማ ከተማ በዋናነት በመድረሰቱል ኸይርያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የሙኒር መስጂድ ኢማም ሼህ መሀመድ አባተማም ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓሉን ስናከብር የነቢዩን አስተምህሮት በማስታወስ ለአቅመ ደካሞች ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

በዓሉ ከሰዓት በኋላ በከተማዋ ቁባ አባ አረቢ በድምቀት የሚከበር ይሆናል፡፡

በአብዱረህማን መሀመድ