አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ከቁጥር ባለፈ ማህበረሰቡን በተግባር ተጠቃሚ ያደረጉ ውጤቶች ተመዝግበዋል አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።
76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ በተለይም በሰው ኃይል ልማት ረገድ ሰፊ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
ጉባኤው ለኢትዮጵያ የተሻለ የጤና ሥርዓት ትልቅ አጋጣሚ ያሉት ሚኒስትሯ፤ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ሽፋን መሻሻሉን ጠቅሰዋል።
እነዚህ ውጤቶች በቁጥር ከመገለጻቸው በላይ በግንባር ቀደምነት ማህበረሰቡን በተግባር ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጉባኤው በዋናነት በጤናው ዘርፍ ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦት ላይ እንደሚመክር ጠቁመዋል፡፡