አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)የ12 ክፍል ተፈታኞች ውጤታቸውን ዛሬ ከምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ አለ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት። የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆኗል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ያሳውቃል።
result.eaes.et EAES Result Checker | Educational Assessment and Examination Services Official portal to check Ethiopian Educational Assessment and Examination Services (EAES) results online. Enter your Admission Number…