አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ መግባባት ላይ የተደረሰባቸው ሀሳቦች የኢትዮጵያን ውስብስብ ችግሮች የሚፈቱ ናቸው አለ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ኢዜማ በሀገራዊ ምክክሩ ለጠቅላላ ጉባኤ የቀረቡ ስምንቱ አጀንዳዎች እና የውሳኔ ሀሳቦችን ይቀበላል ብለዋል።
የሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውስብስብ ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ በምክክር ለመፍታት አዲስ በር የሚከፍት ስለመሆኑ አንስተው፤ ኢዜማ በሀገራዊ ምክክሩ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በምክክሩ መግባባት ላይ የተደረሰባቸው አጀንዳዎች ለህዝብና ለመንግስት የሚቀርቡበት የትግበራ እና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ኢዜማ ድጋፉን እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡
በምክክሩ መግባባት ላይ የተደረሰባቸው ሀሳቦች የኢትዮጵያን ውስብስብ ችግሮች እንደሚፈቱና ትግበራቸው አስፈላጊውን ሂደት የተከተለ እንዲሆንም ፓርቲው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም መካሄድ የጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል፡፡
በዙፋን ካሳሁን