ፋና ስብስብ

ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል

By sosina alemayehu

August 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ላምሮት በምዕራፍ 23 ከምድብ ሁለት 6 ተወዳዳሪዎች ጋር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።

በቅዳሜው ውድድር የምድብ ሁለት ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር በሁለት ዙር ውድድራቸውን ያቀርባሉ።

በምዕራፉ ፍፃሜ የሚቀሩ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቶላቸዋል።

የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን የሚካሄደውን ውድድር 6 ሰዓት ላይ በሁለቱም የፋና ቴሌቭዥኖችና በሁሉም የፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ

በለምለም ዮሐንስ