የሀገር ውስጥ ዜና

ከተሞችን በማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

By Hailemaryam Tegegn

August 27, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከተሞችን በማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋዓለም ከተማ እንዲሁም በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኙ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማትንና የከተማ ኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

በተጨማሪም በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ጩኮ ከተማ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋም እባ በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘውን የሩፎ ዋኤኖ ሞዴል ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ ከተሞችን ዘመናዊ፣ ማራኪና ለኑሮ ምቹ በማድረግ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቅቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲበቁ የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡