አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፋና 80 ምዕራፍ 5 ውድድር ከነበሩት 16 ቡድኖች መካከል ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻሉት ስምንቱ ብቻ ቀርተዋል።
ለምዕራፍ 5 ፍጻሜ ለመድረስ ከምድብ አንድ ቲ ተስፋ ዘመናዊ ዳንስ ቡድን፣ ነፀብራቅ ዘመናዊ ዳንስ ቡድን፣ ዘውድ ዘመናዊ ዳንስ ቡድን እና ኬ ሐበሻ የባህል ቡድን አልፈዋል።
ከምድብ ሁለት ደግሞ ኢትዮ ኪንግ ዘመናዊ የዳንስ ቡድን፣ ዮዳሔ የባሕል ቡድን፣ ኤዞፕ የባህል ቡድን እና ነፀብራቅ ዘመናዊ የዳንስ እና የውዝዋዜ ቡድኖች ማለፋቸው ይታወቃል፡፡
በምዕራፉ 9ኛ ሳምንት ውድድር ላይ የሁለቱም ምድብ ተወዳዳሪዎች በመዋሃድ 8ቱ ቡድኖች የመጀመሪያውን የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ የሚያደርጉ ይሆናል።
በዕለቱ ፋሲካ አከለ በተጋባዥ ዳኝነት ውድድሩን የምትዳኝ ሲሆን÷ በዚሁ የውድድር ቀን ሁለት ቡድኖች በአንድ ጊዜ ይሰናበታሉ።
ቀሪዎቹ 6 ቡድኖች ደግሞ ሁለተኛውን የግማሽ ፍጻሜ ፍልሚያ ለማድረግና የምዕራፉን ፍጻሜ ለመቀላቀል ዕድላቸውን የሚያሰፉ ይሆናል።
ቀዳሚዎቹ የግማሽ ፍጻሜ ሁለት ተሰናባቾች እነማን ይሆናሉ? ይገምቱ!
ሙሉ ውድድሩን እሑድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን እና በፋና ፕላስ ይጠብቁን፡፡
በሲሳይ ገ/ማርያም