የሀገር ውስጥ ዜና

ከሊባኖስ ተጨማሪ 74 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል

By Meseret Awoke

September 02, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ8ኛው ዙር ከሊባኖስ ወደ ኢትዮጲያ ለመጓዝ ሲጠባበቁ የነበሩ 74 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተዋል፡፡

የትራንስፖርት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን ወደ ሀገር ቤት ለመጓዝ ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የነበሩት ዜጎች ናቸው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት፡፡

ባለፉት ሦስት ቀናት በእስር ቤት የነበሩ፣ የመኖሪያ ፍቃድ ያልነበራቸው፣ በአሰሪዎቻቸው በደል ደርሶባቸው እርዳታ ሲደረግላቸው የነበሩ እንዲሁም የህክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረች

ኢትዮጵያዊት ጨምሮ በአጠቃላይ 329 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በተመሳሳይ ዛሬ ማታ እና በመጭዎቹ ቀናት 81 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ነው ቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡