አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይናዋ ቼንዱ ከተማ አዲስ የካርጎ በረራ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።
አዲሱ የካርጎ በረራ በደቡብ ምዕራብ ቻይና እና አፍሪካ መካከል አዲስ የካርጎ ትራንስፖርት መስመር የከፈተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በምዕራብ ቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክርና የሚደግፍ እንደሆነም የአየር መንገዱ መረጃ አመልክቷል፡፡