አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ክሪስታል ፓላስ ከማንቼስተር ሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት በሴልኸርስት ፓርክ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
ባለፈው ሳምንት በኢትሃድ ስታዲየም ባለቀ ሰዓት በጠባብ ውጤት ያሸነፈው የኤንዞ ማሬስካው ማንቼስተር ሲቲ ይሄንንም ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በአዲስ አሰልጣኝ እና በሽግግር ወቅት የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ ጨዋታውን ድል ማድረግ ከቻለ ከፍ ያለ በራስ መተማመንን ይፈጥርለታል፡፡
ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ በኤቨርተን የደረሰበትን ሽንፈት ለማረምና ከሽንፈቱ ለማገገም በሜዳው እና ደጋፊው ፊት የሚያደርገው ፍልሚያ ጠንካራ ፉክክር ያስመለክታል ተብሎ ይጠበቃል።
በአቤል ነዋይ