የሀገር ውስጥ ዜና

የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ “ጓንዷ” በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

By Mikias Ayele

August 29, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነው “ጓንዷ” በዓል በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡

‎‎የዘንድሮው የጓንዷ በዓል “ጓንዷ ለዘላቂ ሠላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

‎በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እና የተለያዩ ብሔሮች ብሔረሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በአብሮነት ታድመዋል፡፡