አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማሕበረሰቡን በመደገፍና አካባቢን በማልማት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው አለ ፍትሕ ሚኒስቴር።
ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማቱ እና ከአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዱብቲ ከተማ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካሂዷል፡፡
የፍትሕ ሚኒስትር ዴዔታ በላይሁን ይርጋ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች ማሕበረሰቡን በመደገፍና አካባቢን በማልማት ረገድ የላቀ ሚና አላቸው።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ም/ኃላፊ አቶ መለስ አባይነህ በበኩላቸው÷ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማህበራዊና አካባቢ ልማት ረገድ አስፈላጊው መሆኑን ገልጸዋል።
በዱብቲ ከተማ የተተከሉት ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ እና የአአባቢውን ሥነ ምሕዳር ለማስተካከል የሚረዱ በመሆናቸው መንከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማሕበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከር፣ አካባቢን በማልማትና በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን በመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡