የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Yonas Getnet

August 30, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ስም በንጉሥ ሃራልድ 5ኛ  ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ለክቡር ንጉሥ ሃኮን 8ኛ፣ ለንጉሣዊው ቤተሰብ፣ ለኖርዌይ መንግሥትና ሕዝብ እንገልጻለን ብለዋል።

ኖርዌይ የኢትዮጵያ ጽኑ አጋር ናት፤ በዚህ አስቸጋሪ ሰዓትም ከኖርዌይ ሕዝብ ጎን እንቆማለን ሲሉም አመልክተዋል።