አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ የጳጉሜን ወር ቀናትን አከባበር አስመልክተው በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
👉 ጳጉሜን ከሌሎች ወራት የምትለይ ብቻ ሳትሆን ያለፈውን ዓመት ስራችንን የምንገመግምበት፣ የሚቀጥለውን ዓመት ስራችንን የምናቅድበትና ተስፋ የምንሰንቅበት ልዩ ወራችን ናት።
👉 የጳጉሜን ወርን ማክበር ያስፈለገበት ምክንያት በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ቀመር ውስጥ ልዩ ወር እና መለያችን ብቻ መሆኑ ሳይሆን ወሩ መሸጋገሪያ በመሆኑ ነው፡፡
👉 ጳጉሜን የአመቱን ሀገራዊ ስኬቶች የምንገመግምበት፣ ክፍተቶችን የምናርምበት እንዲሁም ለቀጣይ ዓመታት አቅጣጫ የምንተልምበት ነው፡፡
👉 የጳጉሜን ቀናትን የምናከብረው በተጨማሪ ዜጎች የግል እቅዳቸው ከሀገራዊ እቅድና አቅጣጫ ጋር እንዲያስተሳስሩና በሀገራችን ሁለተናዊ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ግንዛቤ ለመፍጠር ጭምር ነው ።
👉 የዘንድሮው የጳጉሜን ወር አምስቱም ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ይከበራሉ።
👉 በ2018 ዓ.ም የሀገር ማንሰራራት ማሳያ የሆኑ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
👉 2018 ዓ.ም ሁለተናዊ ብልጽግና እና ከፍታን ሊያረጋግጡ የሚችሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተጀመሩበትና የተጠናቀቁበት ነው
👉 በአፍሪካ ትልቁ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ፣ የኒውክሌር ማመንጫ ፕሮጀክት፣ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካም በዚህ ዓመት የተጀመሩ ናቸው።
👉 ዳግማዊ ዓድዋ ተብሎ የሚጠቀሰው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም ተጠናቅቆ ወደ ስራ የገባው በዚሁ ዓመት ነው።
👉 በዚህ 2018 በጀት ዓመት ገቢ የመሰብሰብ አቅማችን አድጓል፤ ከ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል።
👉 ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ስናነጻጽረው ከ600 ቢሊየን ብር ወይም 67 በመቶ ብልጫ አለው።
👉 በሀገራችን ታሪክ ከፍተኛ የሆነው 10.2 ቢሊየን ዶላር ከውጭ ንግድ ገቢ ተገኝቷል።
በሶስና አለማየሁ