የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ሃገራት ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ስራዎች የኢትዮጵያን ተሞክሮ ሊወስዱ  ይገባል- አፍሪካ ህብረት

By sosina alemayehu

September 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተግባራት ላይ ከኢትዮጵያ ተሞክሮ መውሰድ አለባቸው አሉ የአፍሪካ ህብረት የዘላቂ ከባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሃርሰን ንያምቤ።

ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር  የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን በመከላከል ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።

መርሐግብሩ ንጹህ አየርን ጨምሮ ሌሎች ስነ-ምህዳራዊ ጥቅሞችን ከማስገኘቱም በላይ፣ የካርበን ልቀትን በመቀነስ የአየር ሙቀት መጨመርን ለመከላከል እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

አረንጓዴ ዐሻራ የተራቆተ መሬትንና የአካባቢ ስነ ምህዳር እንዲያገግም በማድረግ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዳይሬክተሩ የአፍሪካ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ተግባራት ላይ የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባቸውና በዚህ ረገድም  ከኢትዮጵያ ተሞክሮ መውሰድ እንደሚገባቸው አመልክተዋል።

ኢትዮጵያም ስኬታማ ተሞክሮዎቿን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማካፈል ግንባር ቀደም ሚና መጫወት አለባት ነው ያሉት።