የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለ840 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

By amele Demisew

September 06, 2026

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ840 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አድርጓል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እንዳሉት÷ መጪውን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 840 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ ምግባር ያሳዩና በሕግ በተደነገገው አግባብ የይቅርታ መስፈርትን ያሟሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የሕግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለው በልዩ ሁኔታ የቀረቡ፣ በማረሚያ ቆይታቸው ስለመታረማቸውና ስለመታነፃቸው ማረጋገጫ የቀረበላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የሕግ ታራሚዎች መካከል 56ቱ ሴቶች ሲሆኑ ÷ 784ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።