የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም ለሰሜን ሸዋ ዞን የ5 ሚሊየን ብር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By amele Demisew

September 06, 2026

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ለሰሜን ሸዋ ዞንና ደብረ ብርሃን ከተማ ተማሪዎች 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ሪጅኑ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ “ለነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ከ4 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድጋፍ ያከናወነው፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ም/ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በዚህ ወቅት ÷ ኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በበርካታ ዘርፎች የሚያደርገው ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ሪጅኑ ለዞኑ ተማሪዎች ያደረገው ድጋፍ የሕዝብ ተቋም መሆኑን ያስመሰከረበት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አንተነህ ፋንታሁነኝ በበኩላቸው÷ ተማሪዎች ላይ መስራት ትውልድ ላይ መስራት መሆኑን በመገንዝብ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በአላዩ ገረመው