የሀገር ውስጥ ዜና

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የጽናት ቀንን አከበረ

By sosina alemayehu

September 08, 2026

አዲስ አበባ፣ጳጉሜን 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጳጉሜን 3 – የጽናት ቀን በኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከብሯል፡፡

አየር ኃይሉ የጀግኖችን ፅናት ተላብሶ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት፤ በቁርጠኝነትና በታማኝነት እየተወጣ እንደሚገኝ በመርሐ ግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡

ሠራዊቱ በዲሲፕሊንና በሙያዊ ብቃት እንዲሁም በአንድነት ለተሰጠው አደራና ለዘላቂ ተቋም ግንባታ ጉዞውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ነው የተገለጸው፡፡

የፅናት ቀን የትናንቱን የጀግንነት ታሪክ በማስታወስ አርበኞችና ጀግኖች የሚዘከሩበት እንዲሁም ዛሬ ያለውን የሠራዊቱን ፅናት በማስቀጠል ለሀገር የተገባው ቃል የሚታደስበት የዕምነትና የአደራ ቀን መሆኑም ተገልጿል፡፡