አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በነገው ዕለት በሕንድ መዲና ኒው ዴልሂ መካሄድ ይጀመራል።
በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራቱ መሪዎች ወደ ከተማዋ እየገቡ ይገኛል፡፡
ከጉባኤው አስቀድሞ በሕንድ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አዘጋጅነት የብሪክስ የንግድ መድረክ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን የአባል ሀገራቱ መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛል፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከጉባኤው በፊት በኒው ዴልሂ ተገናኝተው በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሱድ ፐዜሽኪያን፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ እንዲሁም ፕሬዚዳንት ፑቲን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ ምሽት ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡
በቀጣይ ሰዓታት የሌሎች አባል ሀገራቱ መሪዎች እና ተወካዮች ኒው ዴልሂ ይገባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በነገው ዕለት ለሁለት ቀናት የሚቆየው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ በይፋ ይጀመራል፡፡
በሚኪያስ አየለ