የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By sosina alemayehu

September 12, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግን ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ፥ ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በውይይቱም በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ትብብራችንን ማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል ነው ያሉት።