የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

September 13, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የብሪክስ ጉባዔ 2ኛው ቀን ላይ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በውይይታቸውም በዲጂታላይዜሽን፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በመከላከያ መስኮች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መወያየታቸውን ነው የጠቀሱት፡፡