የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ በትምህርቱ ዘርፍ የተገኘው ውጤት በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Yonas Getnet

September 15, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በትምህርቱ ዘርፍ የተገኘው ውጤት በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው አሉ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፡፡

በክልሉ ዓመታዊ የትምህርት ጉባኤ የትምህርቱ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በጉባኤው በክልሉ በመማር ማስተማሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ትምህርት ቤቶችና ባለድርሻ አካላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ በዚሁ ወቅት ÷በ2018 ዓ.ም በትምህርት ዘርፍ የተገኘው ውጤት እንዲጠበቅና የበለጠ እንዲሻሻል ከሁሉም አካላት ተጨማሪ ጥረት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የተገኘው ውጤት የሚያስደስት ቢሆንም፣ ውጤቱን ማስቀጠል ብቻ ሳይሆን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባም ነው የገለጹት ፡፡

የክልሉ አመራርና የትምህርት ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ለአዳዲስ አሰራሮች፣ ለለውጥና ለተሻለ ውጤት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የተገኘው እውቅና ስኬት በቀጣይ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ መነሻ መሆን እንደሚገባውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትም የሀረሪ ክልል 22 ነጥብ 7 በመቶ የማለፊያ ምጣኔ በማስመዝገብ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ መያዙ ተመላክቷል።

በተስፋዬ ኃይሉ