አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት( ኢጋድ) 74ኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በጅቡቲ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ስብሰባ በቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በተቋማዊ ማሻሻያ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ይሆናል።
በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እንዲሁም ሌሎችም የቀጣናው ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ከዋነኞቹ የኢጋድ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ አካላት መካከል አንዱ ሲሆን፣ የተቋሙን እንቅስቃሴዎች የመምራት እና በአባል ሀገራት መካከል ያሉ ትብብሮችን ለማጠናከር ጉልህ ሚና አለው።