የሀገር ውስጥ ዜና

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በበጀት ዓመቱ ከውጭ ምንዛሬ 390 ነጥብ 53 ሚሊየን ዶላር አገኘ

By emebet sisay

September 17, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከውጭ ምንዛሬ 390 ነጥብ 53 ሚሊየን ዶላር አገኘሁ አለ።

 

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀን በወዳጅነት አደባባይ እየተከበረ ይገኛል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት በተለያዩ ዘርፎች ያሳካቸውን ስኬቶች በተመለከተ የተለያዩ ዘርፎች ምክትል ስራ አስፈጻሚዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጣይ የተገኙትን ስኬቶች ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰሩ አመልክተዋል።

 

ግሩፑ በምርት ዕቅድ በበጀት ዓመቱ 67 ነጥብ 11 ቢለየን ብር በማግኘት የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካት ችሏል።

በማዕድን ዘርፍም 6 ነጥብ 47 ቢሊየን ብር በማግኘት የእቅዱን 67 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል።

 

በዝግጅቱ የሚድሮክ የስራ ሃላፊዎች ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፤ በ2018 ዓ.ም የተሻለ የስራ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞች እውቅናና ሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

 

በወንድማገኝ ጸጋዬ