አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2026 የስካይትራክስ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን ለ9ኛ ጊዜ አሸንፏል፡፡
አየር መንገዱ በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ እና በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት ሽልማቶችንም ተቀብሏል።
ከዚህ ታላቅ እውቅና በተጨማሪ አየር መንገዱ በተለያዩ የአገልግሎት ማለትም በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ አገልግሎት አሰጣጥ እና በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ ዘርፍ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
እነዚህ ሽልማቶች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጥራት ያለውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ያላቸውን እምነት እና ታማኝነት ያንፀባርቃሉ።
ዕውቅናው አየር መንገዱ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት፣ ልዩ የደንበኞችን እርካታ ለመጠበቅ እና በዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹ ውስጥ ምርጥ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡
ሽልማቶቹ አየር መንገዱ የአገልግሎቶች እና የአሠራሮች ደረጃ በመጠበቅ ረገድ ያለውን ቁርጠኛነት የሚያረጋግጥ ነው መባሉን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡፡