አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 592 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገ 9 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ዜጎች መካከል 34ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማቀላቀል እየተሰራ ይገኛል፡፡ መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ103 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።