የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ ሕዝብ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው

By Hailemaryam Tegegn

September 21, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋሞ ሕዝብ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዚየም እና የፓናል ውይይት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

“ዮ ማስቃላ ለዘላቂ ሰላማችንና ልማታችን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ሲምፖዚየም ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልሉና የጋሞ ዞን የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ሲምፖዚየሙ የጋሞ ሕዝብ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያና የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ ማስቃላ” አካል ሲሆን፤ ለሕዝቡ የባህልና የቋንቋ ዕድገት ፋይዳ ያላቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ምክክር እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

ሁነቱ የበዓሉን የሰላም፥ የኅብረትና የትብብር እሴቶች በመጠቀም ለአካባቢውም ሆነ ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት የጎላ ሚና እንደሚኖረውም ነው የተገለጸው፡፡

የጋሞ ሕዝብ የዘመን መለወጫ ‘ዮ ማስቃላ’ በዓል በነገው ዕለት በልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በአርባምንጭ ከተማ በልዩ ድምቀት ይከበራል፡፡

በማቱሳላ ማቴዎስ