የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

September 22, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከፊንላንድ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ውይይቱ በሁለትዮሽ የጋራ ፍላጎቶች፣ ቀጣናዊ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ያተኮረ ነው፡፡

በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም በጋራ ፍላጎቶች እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡