አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል” ያሆዴ” በሆሳዕና ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የሀዲያ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነዉ “ያሆዴ” በዓል በየዓመቱ በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል ነው።
በበዓሉ የብሔሩ ተወላጆች ወደ ትዉልድ አካባቢያቸው በማቅናት በዓሉን አይረሴ በሆነ መንገድ በድምቀት ከማክበር ባለፈ ማሕበራዊ መስተጋብራቸውን የሚያጠናክሩበት ነው።
በአከባበሩ የብሔሩ ተወላጆች ባህላዊ ልብሶችን በመልበስ በዓሉን የሚያሳዩ ውዝውዜዎችን እና ትርኢቶችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በበዓሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እንዲሁም የፌደራል፣የክልልና የሀዲያ ዞን አመራሮች ፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።