የሀገር ውስጥ ዜና

የካፋ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሮ” በቦንጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

By tigist gizachew

September 22, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የካፋ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል “ማሽቃሮ” በቦንጋ ከተማ በሚገኘው በበዓሉ ማክበሪያ ስፍራ በቦንጊ ሸምበቶ በድምቀት እየተከበረ ነው።

የካፋ የአዲስ የዘመን መሸጋገሪያ በዓል የሆነው “ማሽቃሮ” የሰላም፣ የአንድነትና የጠንካራ ስራ ባህል ተምሳሌት ነው።

በዓሉ አሮጌውን ዓመት በሰላም አሳልፎ ለአዲሱ ዓመት ያደረሰ ፈጣሪ የሚመሰገንበት፣ ያለፉትን የስራ አፈጻጸሞች በመገምገም፣ የወደፊቱ ዕቅድ የሚነደፍበት ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የአካባቢ ጥበቃ ፋይዳም አለው።

በዓሉ ከልጅ እስከ አዋቂ ያለምንም ልዩነት በአንድነት፣ በአብሮነት፣ በፍቅርና በእኩልነት የሚከበር በዓል ነው።

በበዓሉ ላይ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የካፋ ንጉስና የሚክረቾ አባላት፣ የብሔሩ ተወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው ከአጎራባች ዞኖች የመጡ እንግዶች መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።