የሀገር ውስጥ ዜና

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል

By Hailemaryam Tegegn

September 22, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም ይከበራል አለ የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት፡፡

በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።

የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም