Law and Justice concept. Mallet of the judge, books, scales of justice. Gray stone background, reflections on the floor, place for typography. Courtroom theme.

የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል

By Tibebu Kebede

September 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያለው በምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በሌላ መዝገብ ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

አቃቤ ህግም በችሎቱ ተገኝቶ እጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነድ የሚል እና ለውጡን ተቃርኖ “ለውጡ ከድጡ ወደ ማጡ” የሚል ርእስ የተሰጠው የፖለቲካ ይዘት ያለውና ህገ መንግስቱን ለመናድ አልሞ የተዘጋጀ ሰነዶችን ተከትሎ ክስ ለመመስረት እየመረመረ መሆኑን ለችሎቱ አስረድቷል።