አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅቡቲ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጅቡቲ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
በጅቡቲ ቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ ጋር በጂቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታን ይፋ አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመርሐ ግብሩ ላይ ከታደሙ በኋላም በጅቡቲ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡