አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው ድምጻዊ ዳዊት መኮንን ከ27 ዓመታት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ድምጻዊ ዳዊት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና አባ ገዳዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡
ድምጻዊ ዳዊት መኮንን ከረጅም ዓመታት በኋላ ወደ ሀገሩ መመለስ በመቻሉ ታላቅ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል።
በኢትዮጵያ ቆይታውም ኢሬቻን አስመልክቶ በተዘጋጀው “አን ዱፌን ጂራ” በተሰኘው ኮንሰርት ላይ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለአድናቂዎቹ ያቀርባል፡፡
አርቲስት ዳዊት መኮንን በ1980ዎቹ አን ዱፌን ጂራ፣ ሶለኔ እና በሌሎች የፍቅርና የትግል የሙዚቃ ሥራዎቹ ይታወቃል፡፡