አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ የሚከበረውን የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል፡፡
በዚህም መሰረት ከመስከረም 16 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከ5 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሐ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
👉 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች፣
👉 ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች፣
👉 ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ፣
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለገሃር መብራት ፣
👉 ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ፣
👉 ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት፣
👉 ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ፣
👉 ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።
በተጨማሪም ነገ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው፡፡
ሕብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና 990 ነፃ የስልክ መስመርን መጠቀም እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡