አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከንቲባዋ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!
በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባሕላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮው ሁሉ በዓሉን ስናከብር እንደ ዳመራው በአብሮነት ተደምረን፣ በትብብር፣ በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።
በድጋሚ እንኳን ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳቸሁ!