አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በቱሪዝም ዘርፉ በተከናወኑ በርካታ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፡፡
የቱሪዝም ዘርፍ ጉባዔ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ሰላማዊት ካሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ቱሪዝም ሕዝቦችን በማቀራረብ ብሎም የሀገርን እድገት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
መንግሥትም ይህንን በመረዳት ቱሪዝምን አንዱ የኢኮኖሚ ምሰሶ አድርጎ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን አብራርተዋል፡፡
በዚህም ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው ÷ በተለይም በ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያን በዓለም ዘንድ መነጋገሪያ እንድትሆን ያስቻለ ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።
በ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ” ጉዞ ብዙሃንን በማገናኘት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ነው ያስታወሱት፡፡
በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ጎብኚዎች ኢትዮጵያን የጎበኙ ሲሆን ÷ ከዚህም ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት ሚኒስትሯ ፡፡
በፌቨን ቢሻው