የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል ደመራ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከበረ

By tigist gizachew

September 26, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በላዛሪስት ጽዮን ማርያም ቁምስና እየተከበረ ነው።

በአከባበር ስነስርዓቱ ላይ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች፣ ደናግላን እናቶችና ምዕመናን ተገኝተዋል።

መስቀል በደስታ የሚከበረው ውጤቱን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በቤተክርስቲያኒቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንደራሴ አባ ተስፋዬ ወ/ማርያም ተናግረዋል።

በዓሉ ለሀገራችን ሰላምና አንድነት የምንጸልይበት ነው ያሉ ሲሆን፤ ከባሕላዊና ኃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር የፍቅርና የሰላም መሳሪያ አድርጎ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ