አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ በ7ኛ የጨፌ ሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ የክልሉ አስፈጻሚ አካላትን ሹመት አጽድቋል፡፡
ጨፌው አዲስ በጸደቀው አዋጅ 267/2019 መሰረት ስድስት የምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ሹመቶችን ማጽደቁም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. አብዱረህማን አብደላ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 2. አቶ መስፍን መላኩ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 3. ረሻድ ከማል (ዶ/ር) -በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 4. መንግስቱ በቀለ (ዶ/ር) – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 5. አቶ አህመድ ኢድሪስ – በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ 6. አቶ አህመድ ሃጂ- በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ
7. ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) – የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ 8. አቶ ጉዮ ዋሪዮ- የፍትህ ቢሮ ኃላፊ 9. አብዱልአዚዝ ዳውድ (ዶ/ር) – የገንዘብ ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ ተስፋዬ ቱሉ – የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 11. አብዲ ዩያ (ዶ/ር) – የእቅድና ልማት ቢሮ ኃላፊ 12. ቡልቶሳ ሂርኮ (ዶ/ር) – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
13. ነጻነት ወርቅነህ (ፕ/ር) – የጤና ቢሮ ኃላፊ 14. አቶ ተሾመ ቦጋለ-የግብርና ቢሮ ኃላፊ 15. ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) – የማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ታረቀኝ ቡልልታ- የኢንተርፕራይዝና አንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 17. አደሬ አሰፋ (ዶ/ር) – የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 18. ወ/ሮ መሰረት አሰፋ – የመሬት ቢሮ ኃላፊ
19. ወ/ሮ ሰዓዳ አብዱረህማን- የሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ 20. አቶ ጥላሁን ወርቁ- የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ 21. አያንቱ ጉተታ (ዶ/ር) – የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 22. ወ/ሮ እልዳና ሱሌማን- የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 23. አቶ ቲጃኒ ናስር- የሰላም ቢሮ ኃላፊ 24. ወ/ሮ ሮዛ ቢያ- የባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. ግርማ ረጋሳ (ኢ/ር) – የመስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ 26. ኢንጂነር ሃቢብ ቁምቢ (ኢ/ር) – የመንገድና ሎጂስቲክስ ቢሮ ኃላፊ፤ እንዲሁም 27. ማሪያ ጉታ (ኢ/ር) – የውሃ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል፡፡