የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከአውሮፓ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

By emebet sisay

September 28, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከአውሮፓ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሐፊ አምባሳደር ኦሎፍ ስኮግ እና በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ኅብረት ልዩ ተወካይ አኔት ወበር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነት እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ጨምሮ በበርካታ የቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡