አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሴኔጋል አቻው ጋር በዛሬው ዕለት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ዋሊያዎቹ ከዓመታት በኋላ በሀገራቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ለሚያዘጋጁት የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 10 ተደልድሏል፡፡
ዋሊያዎቹ በመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በሱዳን 1 ለ 0 ሲሸነፉ፤ የሴኔጋል ብሐየራዊ ቡድን በአንጻሩ ከሞዛምቢክ ጋር 1 ለ 1 ተለያይቷል፡፡
በኢትዮጵያ በኩል መስፍን ታፈሰ በቅጣት እንዲሁም በረከት ወልዴ ደግሞ በጉዳት ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጭ ሲሆኑ፤ በሴኔጋል በኩል በካፍ ቅጣት የተጣለባቸው ኢሊማን ኒጃዬ እና ኢስማኤላ ሳር አይሰለፉም፡፡