የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰየመ

By sosina alemayehu

September 30, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባዔ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሰይሟል።

በተጨማሪም የክልሉ ምክር ቤት አቶ ይስሃቅ አብርሃም የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል፡፡

አዲሱ አፈ ጉባኤ የምክር ቤቱን የሕግ አውጪነት፣ የቁጥጥርና የውይይት ሥራዎች በመምራት ለቀጣዩ የሥራ ዘመን ኃላፊነት ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በምክርቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።