የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች

By emebet sisay

October 01, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸመችው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ የጠብ አጫሪነት እና የትንኮሳ ድርጊቶች ምላሽ ለመስጠት በአስመራ፣ ኤርትራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት ወስኗል።

ሚኒስቴሩ በቪየና የዲፕሎማሲ ስምምነትን በመጣስ ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት ፈጥረዋል የተባሉ አስርኤርትራውያን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን እንዲለቁ ትዕዛዝ ሰጥቷዋል።

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ታሪካዊ እና የህዝብ ትስስር እንደምታከብርና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ቁርጠኛ መሆኗን የሚኒስቴሩ መግለጫ ያመለክታል።