የሀገር ውስጥ ዜና

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

By Yonas Getnet

October 03, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት መከበር ጀምሯል፡፡

የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል አከባበር ሥነ ሥርዓትን አባ ገዳዎችና ሃደ ሲንቄዎች በምርቃት አስጀምረዋል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምት ወቅት በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ሁሉን ነገር ለፈጠረው ፈጣሪ (ዋቃ) ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ