የሀገር ውስጥ ዜና

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 701 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ‌

By Yonas Getnet

October 05, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 701 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ‎ ወደ ሀገራቸው ከገቡት ተመላሾች መካከል 26 ህጻናት ሲሆኑ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 32 ታዳጊዎች ይገኙበታል። ‎ ወደ ሀገራቸው ‎ለተመለሱት ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሰራ ይገኛል፡፡ ‎ ‎መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ105 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።