አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
በስብሰባው ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ በሙሉ ድምጽ ሰይሟል፡፡
ወ/ሮ አየለች እሸቴ ለቀጣይ አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ለማገልገል በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ