የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

By emebet sisay

October 05, 2026

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ርዕይ በሚያስብ አእምሮ እና በሚሠሩ እጆች ሲመራ ይሰምራል፣ ይጸናልም አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ።

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ታሪካዊቷን ሀገር ኢትዮጵያን ያገለግሉ ዘንድ የተሳካና ፍሬያማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።