የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

By sosina alemayehu

October 06, 2026

👉 የኢትዮጵያ አንድነትና ህልውና ላይ ያነጣጠሩ ውስጣዊና አካባቢያዊ የባላንጣ ሀሳቦች እንዲሁም ፍላጎቶችን አስቀድመን መለየት፤ በቂ ዝግጅት በማድረግ የነገንም ወደፊት ፈተናዎችን የመመልከት ሁለንተናዊ አቅማችንን ማዳበርና የመፈጸም ክህሎታችንን ማላቅ ተገቢ ይሆናል፤

👉 አሁን ካለው ተሞክሯችን እንደምናየው የመፈጸም አቅማችንን ማጠናከራችን፤ ሳይታሰቡ የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችል ስርዓት ማበጀታችን እንደ ሀገር ፍቱን አካሄድን በጋራ ለማየትና ለመመስከር ችለናል፤

👉 በጥልቅ ሀሳብ መመራት፤ ችግሮችን አስቀድሞ መለየት፤ ፍቱንና ተሻጋሪ መፍትሄ ማዘጋጀት የኢትዮጵያን ብሩህ መንገድ የሚያመላክቱ ናቸው፤

👉 የ2019 የትኩረት አቅጣጫችን ያለፉትን የስራ ክንውኖች በሚገባ የተነተነ፣ ምልዓቱንና ክፍተቶቹን የለየ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ይበልጥ የሚያስከብርና ፈጣን እድገቷን የሚያረጋግጥ ይሆናል፤

👉 እቅድን ለማስፈጸም የሚመደቡ አካላት የህዝብን ፍላጎት ያስቀደሙ፣ የዛሬንና የወደፊት ራዕያችንን ጭምር የሚመለከቱ፣ ጊዜን እንደ አንጡራ ሀብት የወሰዱ፣ ፋይዳውን ከፍ አድርገው የሚረዱ፣ የዋዛ ፈዛዛ ልምምዶችን የሚጠየፉ እንዲሁም ትጋት ያላቸው አገልጋዮች እንዲሆኑ ይጠበቃል፤

👉 ሰላም ለኢትዮጵያ እድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጤነና ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ህብረትን፣ ትብብርንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ይከናወናል፤

👉 ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፤ ትምህርት፣ ጤና እና ማህበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል፤

👉 የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈጻጸም ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሰራል፡፡

#የመደመር_መንግሥት

በመልካም ፈቃዱ