አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና 80 የዳንስ ውድድር ምዕራፍ 5 ወደ ፍጻሜው ደርሷል።
ዮዳሄ እና አፍሮ የተሰኙ ቡድኖች በባሕል፣ ቲ ተስፋ እና ዘውድ በዘመናዊ ዳንስ ለፍጻሜው ደርሰዋል።
በምዕራፍ 5 በተደረጉት የዙር ውድድሮች ቡድኖቹ የፈጠራ ችሎታቸውን፣ የመድረክ ብቃታቸውንና የዳንስ አቅማቸውን አሳይተዋል።
በምዕራፋ 5 ፍጻሜ ሃሳብን በዳንስና ውዝዋዜ ጥበብ ስጋ አላብሰው የላቀ አቅማቸውን የሚያሳዩበት ታላቅ ፍልሚያ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በፍፃሜው የትኛው ቡድን የተሻለ ትዕይንት ይዞ ይመጣል? ክብሩንም ሽልማቱን ማን ይጠቀልላል? የምዕራፉስ ባለታሪክ ማን ይሆን?
በምዕራፍ 5 ፍጻሜ ውድድር ይጠብቁን።
በብርኽቲ ማህተም